የስልጣንና ተግባር ትንተና

በህዝብና በጭነት ትራንስፖርት ፍላጎትና አቅርቦት መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ በተለያየ ጊዜ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፤ የአገልግሎት ደረጃውም ዝቅተኛ ነው፡፡ ከዋና ዋና መንገዶች ውጭ ያሉ ነባር የመኖሪያ ሰፈሮችና አዳዲስ መንደሮች በአብዛኛው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ አይደሉም፡፡ ከተማዋ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ በቆዳ ስፋትና በህዝብ ቁጥር ማደግ ምክንያት በተጨማሪ አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ የትራንስፖርት ባለስልጣን እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ በአዲሱ አደረጃጀት የህዝብና የጭነት ትራንስፖርትን አቀናጅቶ እንዲመራ፣ እንዲያስተዳደር እንዲሁም ወደ አገልግሎቱ የሚገቡ ተቋማትንም ሆነ ግለስብ የማደራጀትና የመምራት ሚና ያለውና አገልግሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ስልቶችን እንዲያስፋፋ ስልጣን የተሰጠው በመሆኑ በአገልግሎት አሰጣጡ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን የመፍታት አቅም ይኖረዋል፡፡

Comments Off on የስልጣንና ተግባር ትንተና

የትራንስፖርት ጥናቶች

በመሆኑም በዘርፉ ያሉትን ችግሮች፣ የችግሮች ምንጮች እንዲሁም መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ሃሳቦችን ቀደም ሲል ዘርፉን አሰመልክቶ ከተጠኑ ጥናታዊ ጹሁፎች በመዳሰስ፣ ከመረጃ መረብ፣ ከመስክ ዕይታ፣ ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ እንዲሁም በየደረጃው ካሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ከተደረጉ ውይይቶች የተገኙ ግብዓቶችን እና ያለበትን ሁኔታ በመፈተሽ በቀጣይ የተገልጋዮችንና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አደረጃጀት፣ የስራ ክፍሎችና የፈፃሚዎች የስራ መዘርዝር፣ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማጥናት አስፈላጊ መሆኑን በመታመኑ ከተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት በመነሳት ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የስራ መዘርዝር፣ ደመወዝና ጥቅማጥቅም ተጠንቶ በክፍል አንድ አጠቃላይ መግቢያ፣ በክፍል ሁለት የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ፣ በክፍል ሶስት ለተቋሙ አዲስ አደረጃጀት ማጥናትና መለየት፣ በክፍል አራት ስራዎችን ማደራጀትና የስራ መዘርዝሮችን፣ በክፍል አምስት የስራ መደብ ምዘና እና…

Comments Off on የትራንስፖርት ጥናቶች

ከተማችን

በከተማችን የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ከህብረተሰቡ ፍላጎት ጋር የማይጣጣምና ብዙ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ የተለያዩ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ በዚህ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ ከከተማው ህዝብ ቁጥርና የእንቅስቃሴ ፍላጎት ጋር ሊመጣጠን የሚችል የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም አሁንም የትራንስፖርት አገልግሎቱን በጥራት፣ ተደራሽ በሆነና በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ እቅም ከከተማዋ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጐት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም፡፡ በከተማው ውስጥ በተለይም በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ዕለት በዕለት እየጨመረ የመጣውን የትራንስፖርት ተጠቃሚውን ሕዝብ ከአቅም በላይ በመጫን ማጨናነቅ፣ የትራንስፖርት ፈላጊውን ህብረተሰብ ረጃጅም ሰልፍ እና እንግልት ማየቱ በቂ ነው፡፡

Comments Off on ከተማችን
  • 1
  • 2