ስራዎችን ማደራጀትና የሚያስፈልገው ሙያና ብቃት

የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የማግኘት ፍላጎት ለማሳካት ህብረተሰቡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በመንገድ ላይ የሚኖረው የቆይታ ጊዜ አሁን ከነበረበት በማሻሻል በቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት 6 ደቂቃ፣ በአውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት 15 ደቂቃ ለማድረስ ተቋሙ እንደ ግብ ይዞታል፡፡ በተጨማሪ ተቋሙ በጥረት ሊደርስባቸው የያዛቸው ግቦች መካከል ትኩረት ተሰጥቶቷቸው ያልነበረውን የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች(facilities) በማልማትና በተገቢው ሁኔታ በማስተዳደር ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፤ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ስምሪት በጥራት ለህብረተሰቡ ማቅረብ ያስችል ዘንድ የቁጥጥር ስርዓቱን በማሻሻል 100 ማድረስ፤ ትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን (facilities) በማሟላትና የተለያዩ የትራንስፖርት ዓይነቶችን በመጠቀም ቀደም ሲል የነበረውን የትራንስፖርት ተደራሽነት የጉዞ ጊዜ ወደ 15 ደቂቃ ማሳጠር፤ በተመረጡ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊና የተሟላ…

Comments Off on ስራዎችን ማደራጀትና የሚያስፈልገው ሙያና ብቃት

የስራ መዘርዝር

የትራንስፖርት ባለስልጣን የተሰጠውን ራዕይን ለማሳካትና ተልዕኮውን ለመወጣት በአራት ዋና ዋና የስራ ክፍሎች የተደራጀ ሲሆን እነዚህም የተቀናጀ መረጃና ሲስተም ጥናት ዋና የስራ ሂደት፣ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት (facilities) ልማትና አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት፣ የተቀናጀ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አደረጃጀት፣ ስምሪትና ክፍያ ዋና ስራ ሂደት እና የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት ስምሪትና ከባቢ ጉዳዮች ቁጥጥር ሲሆኑ በዋነኛነት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላት የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት መነሻ በማድረግ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ፣ ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ከአከባቢ ጋር ተስማሚ የሆነና አቅምን ያገናዘበ የትራንስፖርት አገልግሎት በከተማችን እንዲኖር ለማድረግ ያስችላሉ ተብለው የታሰቡ ናቸው፡፡ ተቋሙና የእነዚህ የስራ ሂደቶች አጠቃላይ የስራ ፍሰት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

Comments Off on የስራ መዘርዝር

የትራንስፖርት ሲስተም ጥናት ዘርፍ

በከተማችን የትራንስፖርት ፍላጎትና አቅርቦት የሚጣጣምበት፤ ጥራት ያለው የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚኖርበትንና የሚሻሻልበት ሁኔታ፤ የመስመር፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ እና የቦታ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የክፍያ አገልግሎቶች ቅንጅታዊ አሰራርን (physical, operational and fare integration) ጥናት ማካሄድ እንዲሁም የኦፕሬተሮች የሙያ ፈቃድ መመዘኛ መስፈርቶችን፣ ከህዝብና ከጭነት ትራንስፖርት ጋር ተያያዥ የሆኑ መመሪያዎችንና ማኑዋሎችን ማውጣትና ማፀደቅ፣ በተካሄዱ ጥናቶችና በተዘጋጁ መመሪያዎች ላይ ስልጠና መስጠት እና የተጠኑ ጥናቶች ተግባራዊ መደረጋቸው መከታተል፣ የተገኙ ውጤቶችን መገምገም በዚህ የስራ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡ በዚህ የስራ ክፍል የሚከናወነው የትራንስፖርት መረጃ ማደራጃና መተንተኛ ዘዴዎች፣ ሶፈትዌሮችና ፕሮግራሞችን በማጎልበት እና የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን ሊያቀላጥፉ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የትራንስፖርት መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማጠናቀር፣ መተንተን፣ ማሰራጨት እና የመረጃ…

Comments Off on የትራንስፖርት ሲስተም ጥናት ዘርፍ
  • 1
  • 2