የትራንስፖርት ጥናቶች

የትራንስፖርት ጥናቶች

በመሆኑም በዘርፉ ያሉትን ችግሮች፣ የችግሮች ምንጮች እንዲሁም መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ሃሳቦችን ቀደም ሲል ዘርፉን አሰመልክቶ ከተጠኑ ጥናታዊ ጹሁፎች በመዳሰስ፣ ከመረጃ መረብ፣ ከመስክ ዕይታ፣ ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ እንዲሁም በየደረጃው ካሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ከተደረጉ ውይይቶች የተገኙ ግብዓቶችን እና ያለበትን ሁኔታ በመፈተሽ በቀጣይ የተገልጋዮችንና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አደረጃጀት፣ የስራ ክፍሎችና የፈፃሚዎች የስራ መዘርዝር፣ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማጥናት አስፈላጊ መሆኑን በመታመኑ ከተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት በመነሳት ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የስራ መዘርዝር፣ ደመወዝና ጥቅማጥቅም ተጠንቶ በክፍል አንድ አጠቃላይ መግቢያ፣ በክፍል ሁለት የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ፣ በክፍል ሶስት ለተቋሙ አዲስ አደረጃጀት ማጥናትና መለየት፣ በክፍል አራት ስራዎችን ማደራጀትና የስራ መዘርዝሮችን፣ በክፍል አምስት የስራ መደብ ምዘና እና በክፍል ስድስት የደመወዝ ደረጃን በማካተት የጥናት ሰነዱ ተዘጋጅቷል፡፡