የትራንስፖርት ሲስተም ጥናት ዘርፍ

የትራንስፖርት ሲስተም ጥናት ዘርፍ


በከተማችን የትራንስፖርት ፍላጎትና አቅርቦት የሚጣጣምበት፤ ጥራት ያለው የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚኖርበትንና የሚሻሻልበት ሁኔታ፤ የመስመር፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ እና የቦታ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የክፍያ አገልግሎቶች ቅንጅታዊ አሰራርን (physical, operational and fare integration) ጥናት ማካሄድ እንዲሁም የኦፕሬተሮች የሙያ ፈቃድ መመዘኛ መስፈርቶችን፣ ከህዝብና ከጭነት ትራንስፖርት ጋር ተያያዥ የሆኑ መመሪያዎችንና ማኑዋሎችን ማውጣትና ማፀደቅ፣ በተካሄዱ ጥናቶችና በተዘጋጁ መመሪያዎች ላይ ስልጠና መስጠት እና የተጠኑ ጥናቶች ተግባራዊ መደረጋቸው መከታተል፣ የተገኙ ውጤቶችን መገምገም በዚህ የስራ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡

በዚህ የስራ ክፍል የሚከናወነው የትራንስፖርት መረጃ ማደራጃና መተንተኛ ዘዴዎች፣ ሶፈትዌሮችና ፕሮግራሞችን በማጎልበት እና የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን ሊያቀላጥፉ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የትራንስፖርት መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማጠናቀር፣ መተንተን፣ ማሰራጨት እና የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱም አጠቃላይ ደህንነቱን መከታተልና መጠበቅ ነው፡፡