የስራ መዘርዝር

የስራ መዘርዝር

የትራንስፖርት ባለስልጣን የተሰጠውን ራዕይን ለማሳካትና ተልዕኮውን ለመወጣት በአራት ዋና ዋና የስራ ክፍሎች የተደራጀ ሲሆን እነዚህም የተቀናጀ መረጃና ሲስተም ጥናት ዋና የስራ ሂደት፣ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት (facilities) ልማትና አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት፣ የተቀናጀ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አደረጃጀት፣ ስምሪትና ክፍያ ዋና ስራ ሂደት እና የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት ስምሪትና ከባቢ ጉዳዮች ቁጥጥር ሲሆኑ በዋነኛነት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላት የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት መነሻ በማድረግ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ፣ ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ከአከባቢ ጋር ተስማሚ የሆነና አቅምን ያገናዘበ የትራንስፖርት አገልግሎት በከተማችን እንዲኖር ለማድረግ ያስችላሉ ተብለው የታሰቡ ናቸው፡፡ ተቋሙና የእነዚህ የስራ ሂደቶች አጠቃላይ የስራ ፍሰት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡