የስልጣንና ተግባር ትንተና

የስልጣንና ተግባር ትንተና

በህዝብና በጭነት ትራንስፖርት ፍላጎትና አቅርቦት መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ በተለያየ ጊዜ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፤ የአገልግሎት ደረጃውም ዝቅተኛ ነው፡፡ ከዋና ዋና መንገዶች ውጭ ያሉ ነባር የመኖሪያ ሰፈሮችና አዳዲስ መንደሮች በአብዛኛው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ አይደሉም፡፡ ከተማዋ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ በቆዳ ስፋትና በህዝብ ቁጥር ማደግ ምክንያት በተጨማሪ አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ የትራንስፖርት ባለስልጣን እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ በአዲሱ አደረጃጀት የህዝብና የጭነት ትራንስፖርትን አቀናጅቶ እንዲመራ፣ እንዲያስተዳደር እንዲሁም ወደ አገልግሎቱ የሚገቡ ተቋማትንም ሆነ ግለስብ የማደራጀትና የመምራት ሚና ያለውና አገልግሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ስልቶችን እንዲያስፋፋ ስልጣን የተሰጠው በመሆኑ በአገልግሎት አሰጣጡ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን የመፍታት አቅም ይኖረዋል፡፡