ከተማችን

ከተማችን

በከተማችን የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ከህብረተሰቡ ፍላጎት ጋር የማይጣጣምና ብዙ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ የተለያዩ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ በዚህ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ ከከተማው ህዝብ ቁጥርና የእንቅስቃሴ ፍላጎት ጋር ሊመጣጠን የሚችል የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም አሁንም የትራንስፖርት አገልግሎቱን በጥራት፣ ተደራሽ በሆነና በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ እቅም ከከተማዋ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጐት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም፡፡ በከተማው ውስጥ በተለይም በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ዕለት በዕለት እየጨመረ የመጣውን የትራንስፖርት ተጠቃሚውን ሕዝብ ከአቅም በላይ በመጫን ማጨናነቅ፣ የትራንስፖርት ፈላጊውን ህብረተሰብ ረጃጅም ሰልፍ እና እንግልት ማየቱ በቂ ነው፡፡