ስራዎችን ማደራጀትና የሚያስፈልገው ሙያና ብቃት

ስራዎችን ማደራጀትና የሚያስፈልገው ሙያና ብቃት

የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የማግኘት ፍላጎት ለማሳካት ህብረተሰቡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በመንገድ ላይ የሚኖረው የቆይታ ጊዜ አሁን ከነበረበት በማሻሻል በቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት 6 ደቂቃ፣ በአውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት 15 ደቂቃ ለማድረስ ተቋሙ እንደ ግብ ይዞታል፡፡ በተጨማሪ ተቋሙ በጥረት ሊደርስባቸው የያዛቸው ግቦች መካከል ትኩረት ተሰጥቶቷቸው ያልነበረውን የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች(facilities) በማልማትና በተገቢው ሁኔታ በማስተዳደር ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፤ የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ስምሪት በጥራት ለህብረተሰቡ ማቅረብ ያስችል ዘንድ የቁጥጥር ስርዓቱን በማሻሻል 100 ማድረስ፤ ትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን (facilities) በማሟላትና የተለያዩ የትራንስፖርት ዓይነቶችን በመጠቀም ቀደም ሲል የነበረውን የትራንስፖርት ተደራሽነት የጉዞ ጊዜ ወደ 15 ደቂቃ ማሳጠር፤ በተመረጡ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊና የተሟላ የትራንስፖርት መረጃ ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግና የመረጃ አቅርቦቱን 100 ማድረስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡